የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሎላንድ ኝበር፤ የአካባቢው ማህበረሰብ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግብና ምግብ ነክ ነገሮችን ለይቶ የመጠቀም ልምዱ ያልዳበረ በመሆኑ ከግንዛቤ ስራው ባሻገር በወረዳው ግብረሃይል በማቋቋም በጋራ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የማህበረሰቡን ጤና የሚጎዱ የተለያዩ የለስላሳ መጠጦች የታሸጉ የፋብሪካ ወተት እና ጁስ እንዲሁም የተበላሸ ዱቄት የማስወገድ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የዳሰነች ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኢርቂሁን ገመዳ በበኩላቸው፤ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶችን ከግብረሃይሉ ጋር በመሆን ከሚሰራው የማስወገድ ስራ በተጨማሪ ጊዜያቸው ሊያልፍ 6 ወር የቀራቸው መድሃኒቶች ከመበላሻታቸው በፊት ከቱርሚ ጤና ጣቢያ ጋር በመነጋገር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የዳሰነች ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከልና ኦፕሬሽን አመራር ምክትል ሳጅን ዳንኤል ካሣ፤ ፖሊስ በማህበረሰቡ ላይ አደጋ ከመድረሱ በፊት መከላከል አንዱ ተግባሩ በመሆኑ ከግብረ ሃይሉ ጋር በጋራ በመሆን የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ነገሮችን ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የማስወገድ ስራ እየተሰራ እንዳለ ገልፀዋል።
አስተያየታቸውን ከሰጡን መካከል የተለያዩ የለስላሳ መጠጦችና የታሸጉ ወተትና ጁስ አከፋፋይ የሆኑት አቶ ጳውሎስ ጌታ፤ ግብረ ሃይሉ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምርቶችን በሳምንት ሁለት ጊዜ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናግረው እሳቸውም ለማህበረሰቡ የሚያቀርቡትን ምርቶች የተመረቱበትን ጊዜ እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው መች እንደሚያበቃ አረጋግጠው እንደሚያከፋፍሉ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በክልሉ በተያዘው የበልግ ወቅት በኩታገጠም ሩዝና በቆሎ እያለሙ ያሉ አርሶአደሮች ተስፋ ሰጪ የሆነ የምርት ውጤት እንድናይ አስችሎናል አሉ።
ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና የምርምር ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ አስታወቀ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ዕቅድ አፈፃፀም መገምገም ጀመረ