ሀዋሳ፡ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በቤንች ሸኮ ዞን የኩታ ገጠም ምርትን ከማስፋፋት ባለፈ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በ90 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሙዝ እየተመረተ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊና አማካሪ አቶ ዮሐንስ መላኩ፥ በዞኑ እየተከናወነ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ የ60 በ40 የፍራፍሬ ልማት 60 በመቶ ከሚበሉ ፍራፍሬዎች የሙዝ ክላስተሮችን ማየታቸው የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።
በዞኑ የሚከናወኑ የግብርና ልማት ሥራዎች ሁሉም ወረዳዎች በሚባል ደረጃ ከ90 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ሙዝ በክላስተር እየለማ ከመሆኑም ባለፈ በምርታቸው የተሻለ ገቢ ያላቸውን አርሶ አደሮችን ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ ተናገረዋል።
አርሶ አደሩ በሚያመርታቸው ምርቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የመንገድ መሠረተ ልማት እንዲከናወን የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን አቅጣጫ መስጠቱን የገለፁት አቶ መስፍን፥ ዞኑ በብዛት የኤክስፖርትና ለማዕከላዊ ገቢያ የሚቀረቡ ሰብሎችን የሚያለማ በመሆኑ ለመንገድ ሥራ ትኩረት ያስፈልጋል ብለዋል።
በየጊዜው የአርሶ አደሩ ግንዛቤ እያደገ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በወረዳው ከ13ሺህ ሄክታር በላይ የሙዝ ምርት ከመኖሩም ባሻገር በሳምንት ከ60 እስከ 70ሺህ በዓመት ደግሞ ከ 1 ሚሊዬን ብር በላይ የሙዝ ምርታቸውን የሚሸጡ አርሶ አደሮች እንዳሉም የደቡብ ቤንች ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና የግብርና አካባቢ ጥበቃ ህብረት ስራ ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኪዳነ ሽቅ አስረድተዋል።
ካነጋገርናቸው የሙዝ አምራቾች መካከል በጉብኝት ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡን አርሶ አደር ዳይዳ ጌርኩራ፥ ተገቢው እንክብካቤ ከተደረገ የተሻለ ምርት እንደሚያገኙና በግማሽ ሄክታር መሬት የሙዝ ማሳ ላይ ከ8ሺህ ብር በላይ ገቢ እንደሚያገኙ ተናገረዋል።
ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የማህበረሰቡን ጤና ለማስጠበቅ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች እንዲሁም መድሃኒቶችን በመከታተል እንደሚወገዱ የዳሰነች ወረዳ አስታወቀ
በቀቤና ልዩ ወረዳ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተያዘዉ በጀት አመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዉሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ገለፀ
ትምህርት ቤቶችን በትምህርት ግብዓቶችንና ቁሳቁስ ማደራጀት ለትምህርት ሥራ ውጤታማነት ያግዛል – ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ