ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ የከተሞችን የውስጥ ገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የከተሞችን የውስጥ ገቢ አቅም በማሳደግ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረደ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ለከተሞች ልማት እየተሰሩ ባሉ ስራዎች የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ያነገገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ገልጸዋል፡፡
የሁልባራግ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አሊዬ ናሲር እነደገለፁት የከተሞችን የውስጥ ገቢ በማሰደግ ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ባስቆጠሩት ዕድሜ ልክ ከተሞች ላለማደጋቸው ምክንያት የሆነውን የውስጥ ገቢ ችግር በመቅረፍ ረገድ ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በወረዳው የኬራቴ ከተማን ለማሰደግ ከሚሰሩ በርካታ የመሰረተ ልማት ስራዎች ውስጥ የመንገድ ከፈታና የሬዳሽ ስራ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት፣ በኢንቨስትመንት መሬት ወስደው አጥረው ያስቀመጡ ባለ ሀብቶች እንዲያለሙ ማድረግና የከተማ ፕላን ማሻሸል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡
በወረዳው እንደ ሀገር በተያዘው ኮሪደር ልማት መነሻ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታ ፕሮጀክት 56 ሚሊየን ብር የገቢ አሰባሰብ ሥራ እተሰራ መሆኑንም ኃላፊው አክለው ገልፀዋል፡፡
የኬራቴ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ እብራሂም መሀመድ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የከተማዋን የውስጥ ገቢ አቅም በማሳደግ ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ እና ማራኪ ለማድረግ እንዲሁም ወደ ፈርጅ ሦስት ከተማ ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከተማዋን ለማልማት በሚሰሩ ሥራዎች የህብረተሰብ ተሳተፎ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን እና በየጊዜ ከተማዋን የማፅዳት ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
አቶ ቱግባር ሱንከሞ እና ወይዘሮ ረዲና ከዲር በወረዳው ኬራቴ ከተማ በፅዳት ስራ ተሰማርተው ሲሰሩ አግኝተን ካነገገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ሲሆኑ ከተሞችን ለማሳደግ እየተሰሩ ባሉ ተስፋ ሰጪ የልማት ሥራዎች የህብረተሰቡ እገዛ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከተማዋ በፊት በነበረባት የመሠረተ ልማት ችግር ለአኗኗር ምቹ ሁኔታ እንዳልነበራትና በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የመሰረተ ልማት ሥራዎች መሠራተቸውን እና እያደገች መሆኑን የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል፡፡
በልማት ስራዎቹ በመሳተፍ ለከተሞች ልማት በሚደረጉ ጥረቶች የድርሻቸውን እንደሚወጡም በመጠቆም።
ዘጋቢ: ሳጅዳ ሙደስር – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
የማህበረሰቡን ጤና ለማስጠበቅ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች እንዲሁም መድሃኒቶችን በመከታተል እንደሚወገዱ የዳሰነች ወረዳ አስታወቀ
በቀቤና ልዩ ወረዳ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተያዘዉ በጀት አመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዉሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ገለፀ
የኩታ ገጠም ምርትን ከማስፋፋት ባለፈ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በ90 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሙዝ እየተመረተ መሆኑ ተገለፀ