ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ሚና እንዳለቸው ተገለፀ
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በቢጂአይ ኢትዮጵያ ዘቢዳር ቢራ ፋብሪካ ድጋፍ ከ11 ሚልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የጋሶሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ተመርቋል።
በምርቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንደገለጹት፤በዞኑ የትምርት ጥራት ለመሻሻል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህም በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ባለፈው በጀት አመት ከዞኑ ማህበረሰብ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ገንዘብ ተሰብስቦ መፅሃፍ መታተሙንም አስታውሰዋል ዋና አስተዳዳሪው።
በዛሬው ዕለትም በቢጂአይ ኢትዮጵያ ተገንብቶ የተመረቀው ት/ቤት ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ያሉት አቶ ላጫ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ለተወጣው ማህበራዊ ሃላፊነትም አመስግነዋል።
ትምህር ለትውልድ ስነ-ምግባርና እውቀት መጎልበት ከላው ከፍተኛ ፋይዳ አንፃር ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት መላክና በተገቢው መከታተል ይገባቸዋልም ብለዋል።
የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር በበኩላቸው፤ የብልፅግና መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው ዘርፎች አንዱ ትምህርት መሆኑን ገልፀው ለዚህም አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ቀርፆ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ አመላክተዋል።
ቢጂአይ ኢትዮጵያ ዘቢዳር ቢራ ፋብሪካን ፈለግ በመከተል ሌሎች ድርጅቶችም መሰል ተግባራት ላይ በትኩረት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ሲኤስ አር ዳይሬክተር አቶ በሃይሉ አየለ እንዳሉት፤ ትምህርትና የሃይል አቅርቦት ለማህበረሰብ ልማት መሰረታዊ መሳሪያዎች ናቸው።
በመሆኑም ቢጂአይ ኢትዮጵያ ትምህርት፣ ጤና እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራባቸው የሚገኙ የማህበረሰብ አቀፍ ተግባራቶች መሆናቸውን በማውሳት በማስፋፊያው የተገነባው የጋሶሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ከ11 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 8 መማሪያ ክፍሎች ያሏቸው 2 ብሎኮች እያንዳንዱ ክፍል ከ50 እስከ 60 ተማሪዎችን መያዝ የሚችል ደረጃውን የጠበቀ ግንባታ እንደሆነም ነው የገለጹት አቶ በሃይሉ።
የት/ቤቱ የተማሪ ወላጆች መካከል አቶ መሃመድ አህመድ እና አቶ ረሻድ ድንቁ በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ ቀደም ልጆቻቸው ይማሩባቸው የነበሩ ክፍሎች ምቹ ባለመሆናቸው ወደ ት/ቤት ሲልኳቸው ፍቃደኛ እንዳልነበሩና አሁን ላይ ደረጃቸውን የጠበቀ መማሪያ ክፍሎች በመገንባቱ ደስተኛ ሆነው እየተማሩላቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ትምህርት ቤታቸው በአዲስ መልክ ተገንብቶ በማየታቸው እንዳስደሰታቸውና ንፁህና መቀመጫ ወንበሮች በተሟላለት ክፍል ላይ መማራቸው ውጤታማነታቸው ላይ አስተዋፅኦ እንዳለው በጋሶሬ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነኢማ ሱልጣን እና የ8ኛ ክፍል ተማሪ አብዲ ከድር ተናግረዋል።
ከዚሁ ጎን ለጎን ከ2 ሚልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የትራንስፎርመር ምረቃ ስነ-ስርአትም ተከናውኗል።
ዘጋቢ፡ ሚፍታ ጀማል – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በ2017 በጀት ዓመት ከ3 መቶ ሺ በላይ አዲስ አባላትን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል – የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የሆሳዕና ክላስተር
የማህበረሰቡን ጤና ለማስጠበቅ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ምግብና ምግብ ነክ ነገሮች እንዲሁም መድሃኒቶችን በመከታተል እንደሚወገዱ የዳሰነች ወረዳ አስታወቀ
በቀቤና ልዩ ወረዳ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በተያዘዉ በጀት አመት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዉሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ገለፀ