በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራ የአመራሮች ቡድን በአርባምንጭ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራትን ምልከታ አድርጓል
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢፌዴሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራ የአመራሮች ቡድን በአርባምንጭ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችንና የልማት ኢኒሼቲቮችን ምልከታ አድርጓል።
ቡድኑ በአርባምንጭ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት፣ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የአርባምንጭ ከተማ ሁለገብ ስታዲየም ግንባታ እና በቅርቡ የተመረቀውን የጋሞ አደባባይ ተመልክተዋል።
በተጨማሪም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ እናት ሞሪንጋ ኢንተርፕራይዝ እና ያላ አግሮ ኢንዱስትሪ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጎብኝተዋል።
በግንባታ ላይ የሚገኘው ስታዲየም የካፍ እና ፊፋ ስታንዳርዶችን ባሟላ መልኩ መገንባት እንዳለበትና አለምአቀፍ ወድድሮችን ወደ ከተማው ለማምጣት በሚያስችል አግባብ ሊሆን እንደሚገባ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።
ቡድኑ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ለዞኑ እንዲሁም ለከተማዉ አመራሮች ግብረመልስ እንደሚሰጥ እንደሚጠበቅ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
More Stories
በአርብቶ አደር አከባቢዎች የሴቶች የትምህር ተሣትፎ እያደገ መምጣቱ ተገለፀ
ለካሳ ክፊያ ይወጣ የነበረውን 700 ሚሊዮን ብር ማዳን መቻሉን የዲላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ገለጸ
ዋካን ለማልማት በማንኛውም ተሳትፎ ከከተማዋ አስተዳደር ጎን እንደሚቆም በዳውሮ ዞን የማረቃ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ