በከተሞች የተጀመረውን ኮሪደር ልማትን ለማፋጠን ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚፈልቁ የፈጠራ ውጤቶች ሥራውን ለማሳለጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ተገልጿል።
የከተሞች የኮሪደር ልማት በተሳካ መልኩ ለማልማትና ለማፋጠን ወጣቶች በተለያዩ ሙያ ዘርፎች እየሰለጠኑ መሆናቸውን በኣሪ ዞን የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው ተናገረው፤ በተቋሙ በተለያዩ ቴክኖሎጂ ዘርፎች የሽግግር ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገለፀዋል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን አክለው በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር የሚገቡ አብዛኛውን የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ፈጠራ ሥራዎች መተካት እንደሚቻል በኮሌጁ እየተሰሩ ያሉ የፈጠራ ወጤቶች ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የማኑፋክቸሪንግ ትምህርት ክፍል ኃላፊና የፈጠራ ሥራዎች ባለሙያና አሰልጣኝ መምህር ጉማሌ ኩራሽሶ በበኩላቸው፤ በኮሌጁ በርካታ የፈጠራ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው ለከተማው ኮሪደር ልማት አጋዥ የሆኑ የመብራት ፖሎችና ሌሎች የፈጠራ ሥራዎች እየተመረቱ ይገኛሉ ብለዋል።
በተቋሙ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ያነጋገርናቸው ወጣቶችም በሥራው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቁመው ሙያውን እንድንቀስምና ወደፊት በኢኮኖሚ እራሳችንን እንዳንችል አቅም እያገኘን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በሀገር ውስጥ ያሉ ዕምቅ ሀብትን በመጠቀም የተሻለ አካባቢ ለመገንባትና ለወጣቱ ሥራ ዕድል ለመፍጠር የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡ ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ተቀራርቦ በጋራ መሥራት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያዝ ተጠቆመ
የጀፎረ ባህላዊ አውራ መንገድን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የማስተማር አቅም ግንባታ ለትምህርት ባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ