ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ምርቶችን አብዝተዉ በማምረት ኢኮኖሚያቸዉን እያሳደጉ መሆናቸዉን በዳዉሮ ዞን ድሳ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ

ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ምርቶችን አብዝተዉ በማምረት ኢኮኖሚያቸዉን እያሳደጉ መሆናቸዉን በዳዉሮ ዞን ድሳ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 24/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ምርቶችን አብዝተዉ በማምረት ኢኮኖሚያቸዉን እያሳደጉ መሆናቸዉን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳዉሮ ዞን ድሳ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡

የቅመማ ቅመም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ 5መቶ 25 ሄክታር ማሳ በቅመማቅመም ሰብሎች መሸፈኑን የወረዳዉ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የዳዉሮ ዞን ድሳ ወረዳ ከፍተኛ የቅመማቅመም ምርት አምራችና  ለገበያ ከሚያቀርቡት ወረዳዎች አንዱ ሲሆን በተለይም በመድኃኒትነት ባህሪ  ያለዉና እና አገር በቀል ቅመማቅመም አምራች ወረዳ ነዉ።

አርሶ አደር አሮታ አልሎ የድሳ ወረዳ ማልዲጢ ማሹንቻ ቀበሌ ነዋሪ  ሲሆኑ ለበርካታ ዓመታት  አንድ ሄክታር በላይ መሬት ላይ  አርቲ በማልማት በሚየገኙት ገቢ ልጆቻቸዉን በማስተማር፣ ባጃጅ ሞተር በመግዛት፣ ከሁለት በላይ ቤት በመሥራት ኢኮኖሚያቸዉን ማሳደግ መቻላቸዉን ተናግረዋል።

የጋቶ ጉፎ ቀበሌ አርሶ አደሮች መካከል አርሶ አደር ባትሳ በቀለ እና መስፍን ሰማ እንደተናሩት፤ ከዚህ በፊት በኤይድ በተሰኘዉ ድርጅት ድጋፍ የተለያዩ ችግኞችን በማፍላት ወደ 1መቶ 96ሺህ ብር በመመግኘት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

አሁን ላይ ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆ በዚሁ ድርጅት ድጋፍ በቡናና ቅመማቅመም ዘርፍ ወደ ጎን 1መቶ ወደ ላይ 18 የሚይዝ  24 የቡና መደብ ገቢ እየተጠባበቁ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

አርሶ አደሮች ገበያ ተኮር የቅመማቅመም ሰብሎች በስፋት በማልማት ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ የግብርና ባለሙያዎች በቅርበት የሙያ ድጋፍና እገዛ እያደረጉላቸው መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በወረዳዉ ግብርና ጽ/ቤት የቅመማ ቅመም ልማት ባለሙያ አቶ ባትሳ በልሎ እንደገለጹት፤ በወረዳዉ ከሚገኙ 16ቱ ቀበሌያት መካከል የማልዲጢ ማሹንቻ ቀበሌ ደልባና ጎሏ ንዑሶች በአርቲ ምርት የሚታወቁ ናቸዉ።

የወረዳዉ አርሶ አደሮች አርቲ፣ ቡና፣ ኮረሪማ፣ ዝንጅብል፣ በርበሬ፣ ዕርድ፣ ድንብላልና  ሌሎችንም የቅመማ ቅመም ሰብሎችን በማልማት ላይ ተሰማርቷል፡፡

ከዚህም በወረዳ ደረጃ 9መቶ 23ሺህ ኩንታል ለማግኘት ታቅዶ በ2ኛ ሩብ ዓመት 23ሺህ 55 መከናወኑን ገልፀዋል።

ሌላዉ ምርቱን ይበልጥ ለማስፋፋት በወረዳዉ ጋቶ ጉፎ ቀበሌ እና አርጋ ቀበሌ ሁለት የቡና ችግኝ ጣቢያዎች ተቋቁመው የተሻለ ምርት የሚሰጡ የቡና ዝርያ በመደብ ከ24 በላይ ችግኞች አርሶ አደሮቹ እየተባዙ መሆኑን አመላተዋል፡፡

ዘጋቢ፡ አባይነሽ ወራቦ – ከዋካ ጣቢያችን