ነባር በዓላት የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ለልማት አቅም ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ

ነባር በዓላት የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ለልማት አቅም ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየአካባቢው የሚከበሩ የህዝብ ነባር በዓላት የህዝቦች አንድነትና አብሮነት በማጠናከር ለሰፊው ልማት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገለፀ።

የኣሪ ብሔረሰብ የ2017 ዓ/ም ድሽታ ግና የዘመን መለወጫ በዓል በዞኑ በዎባ ኣሪ ወረዳ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል።

ወረዳው በዓሉን መነሻ በማድረግ ለመንግስት መሥሪያ ቤት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ለመገንባት የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በማዘጋጀት በዓሉ በድምቀት መከበሩን የዎባ ኣሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ህዝቅኤል ጋርታ ገልፀዋል።

በዓሉን እያከበርን ልማቱን ለማስቀጠል በልዩ ትኩረት እየሠራን ነው ሲሉ አቶ ህዝቅኤል ተናግረዋል።

በወረዳ ደረጃ በዓሉ በተሳካ መልኩ በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁንም አስረድተዋል።

በበዓሉ ቦታ የተገኙት የደቡብ ኦሞ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ ትንሹ ተክሌ፥ የድሽታ ግና በዓል እሴት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሐሳብን የያዘ በመሆኑ በዓሉ የኣሪ ብሔረሰብ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በቀጣይ በዞን ደረጃ የሚከበረው የድሽታ ግና የ2017 ዓ/ም ማጠቃለያ በልዩ ድምቀት እንደሚከበር የገለፁት ሀላፊው በተለይ ለሠላምና አንድነት ቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶ ይከበራል ብለዋል።

የኮሮሪማ፣ የቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንሰት ብሎም የበርካታ ተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት የሆነችው የዎባ ኣሪ ወረዳ ነዋሪዎች ወደ በዓሉ ቦታ ሲመጡ ለወረዳው አስተዳደር ስጦታዎችን አበርክተው በዓሉን አክብረዋል።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን