በአመራሩና በፈጻሚ ደረጃ ያሉ ተግባራትን በተነሳሽነት መስራትና በጤናው ዘርፍ ያሉ ጉድለቶችን መለየት እንደሚገባ ተመላከተ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአመራሩና በፈጻሚ ደረጃ ያሉ ተግባራትን በተነሳሽነት መስራትና በጤናው ዘርፍ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው የእናቶችና ህጻናት ጤናና ስርአተ ምግብ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የአፈጻጻም ግምገማ መድረክ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ እንደገለፁት የህብረተሰቡ ጤና እንዲሻሻል በተለይም የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ አገልግሎቱን ማዘመን ያስፈልጋል።
በጤናው ዘርፍ በተያዘው ሩብ አመት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡንም ተጠቁሟል።
የሚሰጡ ክትባቶችን በጥራት ከመስጠት አኳያ ጠንካራ ክትትል በማድረግ የሚታይ ለውጥ ማምጣት ይገባልም ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።