የደቡብ ኢትዮጵያዊ ክልል ግብርና ቢሮ ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ የተገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም ማምረት እንደሚገባ አመላክቷል።
የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማገሶ ማሾሌ፤ ከበጋ ስንዴ ጋር ተያይዞ ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ከ2015 ጀምሮ በተካሄደው ሥራ 15 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን አስረድተዋል።
በዘንድሮው የበጋ ስንዴ ደግሞ የምርት መጠኑን ወደ 19 ሚሊየን ኩንታል ለማድረስ ይሰራል ነው ያሉት።
ቀደም ሲል በኩንታል 31 ኩንታል ይገኝ የነበረውን ምርት ወደ 34 ኩንታል ለማድረስ ይሰራል ብለዋል።
በዞኑ 1650 ሄክታር መሬት በዘንድሮ የበጋ ስንዴ ምርት ይለማል ያሉት ኃላፊው ግብዓት በተገቢው ሁኔታ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራም አመላክተዋል።
የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ፤ ዞኑ ገና ያልለማ በርካታ ሄክታር የሚሆን መሬት እንዳለው ጠቁመው ይህን መሬትና ቀደም ሲል እየለማ ያለውን መሬት የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃን ተጠቅሞ ማልማት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
በበጋ ስንዴ ዘር ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃ/ማርያም ተስፋዬ፤ ከግብርና ሥራ ጋር በተያያዘ የጋሞ ልማት ማህበር እያደረገ ያለውን ሥራ አመስግነው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲቻል ያሉንን የውሀ አማራጮችን ተጠቅመን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በክልሉ በበጋ መስኖ ስንዴን ጨምሮ 30 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እንደታቀደ ኃላፊው አብራርተዋል
ዘጋቢ፡ ታምሩ በልሁ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በስፖርትና ባህል ልማት ዘርፍ የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አበክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም አደመጠ
ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሠራ የዲላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ