ሀዋሳ፡ ሕዳር 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዓሉን በንግግር የከፈቱት የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ በንግግራቸው በዓሉን ስናከብር አንድ የሚያደርጉንን ሁነቶች በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል
የተዛብ ትርክቶች የህዳሴ ጉዟችንን እንዳያሰናክልብን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የማይታዩ ድንበር ዘለል እጆች በሚጥሯቸው ውጅንብሮች ሳንደናገር አንድነታችንን በማረጋገጥ ሰላማችነንን ማፅናት ይገባናል ብለዋል
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ህገ- መንግስታችን ያጎናፀፈን የእኩልነታችንና የአንድነታችን ማህተም መሆኑን የገለፁት የልዩ ወረዳው ዋና አፈ ጉባዔ ሻምበል ደበሮ ይህንን የብዙሀን የትግል ውጤት ለማፅናት ሁላችንም የሰላም አምባሳደር ልንሆን ይገባናል ብለዋል።
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እርስ በእርስ እንድንተዋወቅ ባህል ወግ ስርዓቶቻችንን እንድናስተዋውቅ እድል የፈጠረ መሆኑን የገለፁት የልዩ ወረዳው ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሊሬ አሌዬ በበኩላቸውም ህብብራዊነት ላስጌጣት ሀገር የብሄር ብሄረሰብ በዓል አላማ በየዕለት ተእለት እንቀሳቀሴያችን ሊተገበር የሚገባው ጉዳይ ነው ብለዋል ።
በዓሉ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና አጉራባች ዞንና ወረዳዋች ከመጡ እንግዶች ጋር በተለያዩ የኪነጥበ ስራዎች በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል
ዘጋቢ : ሰብስቤ አደም

                
                                        
                                        
                                        
                                        
More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ