የአመያ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ ስንዴ የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሠሩ መሆናቸውን ገለፁ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች በበጋ መስኖ ስንዴ የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሠሩ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
በወረዳው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም 400 ሄክታር ማሳ በበጋ መስኖ ስንዴ ለመሸፈን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
በአመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፋ ላሼ ቀበሌ ካሉት አርሶ አደሮች መካከል አርሶአደር አሰፋ ከተማ እና አርሶአደር ዳዋና ዳርጫ ከዚህ ቀደሞ በአከባቢያቸው በበጋ ወቅት ስንዴ የማይመረት ቢሆንም የግብርና ባለሙያዎች በሰጡት ግንዛቤ መሠረት ስንዴን በማሳቸው ሙሉ የግብርና ፓኬጆችን ተጠቅሞ በመዝራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም የሚጠቀሙት የማጋ መስኖ ግድብ አሁን ላይ በመሰበሩ የውሃ ችግር እንዳጋጠማቸው አርሶአደሮቹ ገልፀው ችግሩ እንዲቀረፍላቸው ጠይቀዋል።
ኦፋ ላሼ ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ወራንኮ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሥራ በአርሶአደሩ ዘንድ መነቃቃት እየተፈጠረ መምጣቱን አውስተው አምና ኬሚካልና ሌሎች የስንዴ መከላከያ መድኃኒቶች ችግር ማጋጠሙን የሚናገሩት ባለሙያው መሰል እጥረቶች ዘንድሮም እንዳይፈጠር ብለዋል ።
የአመያ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቢሻው ተስፋዬ በዘንድሮ የበጋ መስኖ ስንዴ በወረዳው የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም 400 ሄክታር መሬት በማልማት 10 ሺ ኩንታል ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል ።
በወረዳው ኦፋ ላሼ ቀበሌ በማጋ መስኖ ግድብ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት በማድረግ እየተነጋገሩ መሆናቸውን ጠቁመው፥ በበጋ መስኖ ስንዴን ማምረት በአጭር ጊዜ የምርት ጭማሪ እንዲኖር የሚያደርግ በመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ለተግባራዊነቱ ሊተጉ እንደሚገባ አቶ ቢሻዉ አሳስበዋል።
ዘጋቢ : ደረጀ ተፈራ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ