የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመንግስትና ልማታዊ ባለሀብቶች የጋራ ትብብር ውጤታማ የሆኑ ተቋማት ተጎበኙ
በልማታዊ ባለሀብቶች የተሠሩ የቆፌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታዎችና የዳራሮ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት አሁናዊ የመማር ማስተማር ሥራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልና በጌዴኦ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ በተደረገላቸው በበዓሉ ታዳሚዎች ተጎብኝተዋል፡፡
የትምህርቱን ዘርፍ ስብራት ለመጠገን መንግስት የጀመራቸውን ጥረቶች ከማስቀጠል አኳያ ልማታዊ ባለሀብቶች የማይተካ ሚና እያበረከቱ በመሆናቸው ያላቸውን ልባዊ አክብሮት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
የግንባታ ሂደቱ እየተፋጠነ የሚገኘው የዞኑ አስተዳደር ህንፃ ጉብኝቱ ከተካሄደባቸው ተቋማት አንዱ ሲሆን ህንፃው ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ምቹ የሥራ አካባቢን ከመፍጠር ባለፈ የዞኑን ገፅታ ከመቀየር አኳያም ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ: ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ባለፉት 3 ወራት በዞኑ የተከናወኑ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም የታየባቸዉ መሆኑ ተገለጸ
አገርን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና የልማት ተደራሽነትን እውን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን አንዳንድ የሀላባ ቁልቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገልጋዮች ተናገሩ