በነዳጅ ምርቶች ስርጭት ላይ የሚታየውን ሕገ ወጥ አሠራር ለማረም በትኩረት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ
በግብይት ወቅት የሚስተዋሉ ሕገ ወጥ አሠራሮችን ለማስተካከል ሕብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
መንግሥት የጀመራቸውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ምክንያት በማድረግ በምርቶች ላይ ያልተገባ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሐላፊ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ አሳስበዋል።
በተለይም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የነዳጅ ምርቶችን በሕገወጥ መንገድ ከማደያዎች በማውጣት የሕብረተሰቡ ቅሬታ እንዲጨምር በሚያደርጉ አካላት ላይ በተደራጀ ሁኔታ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ነውም ብለዋል የቢሮ ሀላፊው።
የወላይታ ዞን ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀይለ ስላሴ፤ በዞኑ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ65 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን ገልጸው ሰሞኑን ደግሞ በዞኑ ኦፋ ወረዳ ገሱባ ከተማ ከኩንቢ ማደያ 11 ሺህ ሊትር ቤንዚን በሦስት መኪናዎች ተጭኖ ሲወጣ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸዋል።
የነዳጅ ምርቶች ፍላጎት መጨመር ጋር በተያያዘ የመጣውን ምርት በአግባቡ ሣያደርሱ ለሕገ ወጥነት መነሻ በሚሆኑ ነጋዴዎች ላይ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን እንዲቀጥል ያነጋገርናቸው ተጠቃሚዎች ጠይቀዋል።
በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ማደያዎች የሚመጣውን ነዳጅ በፍትሐዊነት ተደራሽ እንዲያደርጉ በግብረ ሐይል የቁጥጥር ሥራው እየተካሔደ መሆኑም ታውቋል።
ዘጋቢ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ