ባላፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለጸ
በኮሬ ዞን “የሃሳብ ልዕልና፤ ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ፕሮግራም ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ፤ በእስካሁኑ ጉዟችን የብልጽግና ፓርቲ ለህዝቡ የገባውን ቃል እውን በማድረግ የመለያየት ፖለቲካን በማስቀረት፣ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን በማጎልበት፣ በህዝቦች መካከል የወንድማማችነት እሴት እንዲጎላ እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያሰፈነ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዘንድሮ የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ስናከብር እንደ ኮሬ በዞን የመደራጀት ጥያቄያችን በተመለሰበት ወቅት መሆኑ ለየት ያደርገዋል ያሉት አስተዳዳሪው፤ በዞኑ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን በውጤት አሳጅቦ ለማስቀጠል ሁላችንም በትኩረት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጢሞቴዎስ በቀለ በበኩላቸው፤ የብልጽግና ፓርቲ በአምስቱ የለውጥ ዓመታት የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በመደመር ማዕቀፍ ህዝቡን በማስተባበር እና በማሳተፍ በርካታ ስኬቶችን በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው እንዲሁም በማህበራዊና በውጭ ግንኙነት ዲፕሎማሲ መስኮች እያስመዘገበ የመጣ ፓርቲ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታትን በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በቀጣይም ከተስፋ ወደሚጨበጥ ብርሃን ለምናደርገው ብልጽግና ጉዞ ትልቅ አቅም እንደሆነ ታውቆ የተጀመሩ ስኬቶችን ከማስቀጠል አኳያ ሁላችንም የድርሻችንን በትጋት ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት።
በብልጽግና ፓርቲ የአምስት ዓመታት ጉዞ የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ያተኮረ ሰነድ በኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጢሞቴዎስ በቀለ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል።
ዘጋቢ፡ ለምለም ኦርሳ – ይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ህዝቡን የሚለውጡ ልማቶችን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ
በነዳጅ ምርቶች ስርጭት ላይ የሚታየውን ሕገ ወጥ አሠራር ለማረም በትኩረት እየሠራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ
19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ