19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል፡፡
የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር ዜጎች በልዩነት መካከል አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ እንደሚያግዝ የበዓሉ ታዳሚዎች ገልፀዋል፡፡
የይርጋጨፌ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት የጋ በዓሉን አስመልክቶ ሠነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ የፌደራሊዝም አለመዳበር ብዝሃ ማንነቶችን ማስተናገድ ላይ ክፍተቶችን አምጥቷል፡፡
ይሁን እንጂ ዜጎች ልዩነቶችን እንደ እድል ተጠቅመው የነገዋን ኢትዮጵያ በጋራ መገንባት እንደሚችሉም አብራርተዋል፡፡
የይርጋጨፌ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ታዬ ታደሰ በበኩላቸው፤ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር የሁሉም ብሔር ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ እንዲጎለብት ትልቅ አስተዋውፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።
እንደ አፈ ጉባኤው ገለጻ፤ የይርጋጨፌ ከተማ ከሃያ ስድስት በላይ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት መሆኗን በማብራራት ሁሉም የጋራ ማንነቶችን በማዳበር ልዩነቶችን እንደ ፀጋ በመቀበል ለከተማው እድገትና ሠላም የድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አብነት አበበ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።