ዩኒቨርሲቲው በአካባቢው ከሚገኙና አለማቀፍ ከሆኑ 69 ያክል ተቋማትና ኢንዱስትሪ ማዕከላት ጋር ትስስር ፈጥሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንደስትሪ ተቋማት ጋር በህጋዊ ማዕቀፍ በታገዘ የጋራ ዕቅድ ማስተሳሰር የትምህርት አሰጣጡ በተግባር እንዲደገፍ ከማድረግ አልፎ በምርምር ስራዎችም እንዲጎለብት የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህንኑ እውን ለማድረግ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን ነው በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የጂንካ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዓለማቀፋዊነትና አጋርነት ዳይሬክተር ዶ/ር ኮማንደር መሐመድ ገልጸዋል።
ከተቋማት ጋር የተፈጠሩ ትስስሮች በተናጥል የሚደረገውን ሩጫ ቅንጅታዊ እንዲሆን በማድረግ ያለውን የሰው ሃይል በአግባቡ ለመጠቀም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም አስምረውበታል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አምባ ጩፋ በበኩላቸው ከምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ መስራት ተቋማትን ለጋራ ግብ የጋራ አቅም በመፍጠር የጋራ ውጤታማነትን እንዲረጋገጥ የሚያስል መሆኑን ተናግረዋል።
ስለዚህም ዩኒቨርሲቲው ከተቋማቱ ጋር የመሰረተው ትስስር ከመግባቢያ ሰነድ ፊርማ የተሻገረ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል በትኩረት እየተከናወነ የሚገኝ ተግባር ስለመሆኑም አንስተዋል።
ይህ መድረክም ለተጀመሩ የፕሮጀክት ትግበራ ስራዎች ውጤታማነት የኢንዱስትሪ ተቋማትን ማዕከል የማድረጉ ጅምር ስራ በመፈተሽ ወደ ውጤት ለማሻገር ያለመ መሆኑን ጠቅሰው ባለድርሻ አካላትም የድርሻቸው ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ ቴክኒክና ሙያ ከአጎራባች ዞኖች ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በአቅራቢያ የሚገኙ የምርምር ተቋማትና የኢንደስትሪ ማዕከላት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶችና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተሳታፊዎች ሆነዋል።
ዘጋቢ ፡ ዳኜ ጥላሁን- ከጂንካ ቅርንጫፍ ጣቢያ

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።