የ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት አከበሩ።
ኢትዮጵያ በህዝቦች ብዝሀነት የተመሠረተች በቋንቋ፣ በባህልና በሀይማኖት ረገድ ያላት ልዩነት ውበቷ ሆኖ እነሆ ዘመናትን ተሻግራለች።
የጋሞ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሠላማዊት ቦዳ እንደተናገሩት፤ ልዩነታችን አንድነታችን ነው ስንል የአንዳችን መኖር ለአንዳችኝ ዋስትና እንዲሁም ሀገራችን የተያያዘችውን የብለፅግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ሚናው የላቀ ነው።
ባለፉት 19 አመታት በሀገሪቱ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች አንድነታቸው ተጠብቆ ያላቸውን ባህልና እሴት በማስተዋወቁ ረገድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ሚና ከመጫወታቸው በዘለለ በራሳቸው ቋንቋ ሚዲያውን መጠቀም እንዲችሉ መደረጉ ተሰፋ ሰጪ ተግባር ሆኖ ዘልቋል ብለዋል።
በሌላ በኩል ያሉንን ልዩነቶችን ተጠቅመው የህዝቦችን ነባርና ጠንካራ መስተጋብርን ለግጭትና ለሠላም እጦት የሚጠቀሙ አካላትን የማስገንዘብ፣ የማስጠንቀቅና የህዝቦች አንድነት በጠንካራ አለት ላይ የተገነባ መሠረት እንዲሆን ማሳወቅ ከሚዲያ አካላት ይጠበቃል ብለዋል ወ/ሮ ሠላማዊት።
ወ/ሮ ሠላማዊት አያይዘውም የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ብሔር ብሔረሰቦች ያላቸውን እምቅ የባህል፣ የአኗኗርና ሌሎች እሴቶቻቸውን ቱባውን ሳይለቅ ለአለም ማስተዋወቅ የተሰጣቸው ሀገራዊ አደራ ስለመሆኑም አስገንዝበዋል።
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአርባ ምንጭ ከተማ ሲከበር እንግዶች በሚኖራቸው ቆይታ የማይረሳ ትውስታ ይዘው ይመለሱ ዘንድ የሚዲያ ባለሙያዎች ሚና ተኪ የሌለው ነውም ብለዋል።
በመጨረሻም በአሉን የተመለከተ ሠነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ዘጋቢ፡ በኃይሉ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር በብዝሃነት ውስጥ የሚንፀባረቁ የመረዳዳትና የአብሮነት በጎ እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊና የየዞን ከፍተኛ አመራሮች በሣውላ ማረሚያ ተቋም አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ልየታ ተካሄደ