በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ በ85 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የነዳጅ ማዳያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
በዞኑ 429 ባለሃብቶች በግብርና፣በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ መሰመራታቸውም መረጀዎች አመልካቷል ፡፡
በሀዲያ ዞን የሌሞ ወረዳ ዋና አስተደደሪ አቶ ታደለ ደምሴ እንደተናገሩት መንግስት የኢንቨስትመንት እና የንግዱን ማህበረሰብ ለማበረታታትና ለመደገፍ ባለሃብቶች በመረጡት የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል::
የነዳጅ ማደያው ባለቤት አቶ ጌታቸው ገዕናሞ የነዳጅ ማደያው ግንባታ ከ85 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደፈጀ ገልጸዋል::
ለ15 ቋሚና ለ50 ጊዜያዊ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል ፡፡በቀጣይም ከማደያው ጎን ለጎን በኢንዱስትሪ ዘርፍ የፋብሪካ ግንባታ ስራ ለመጀመር ዕቅድ እንዳላቸውም ገልጸዋል ።
የሀዲያ ዞን የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፍ አቶ ታምራት ሜግሶ በበኩላቸው በዞኑ 429 ባለሃብቶች በግብርና፣በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ መሰመራታቸውን ጠቅሰው፣ፕሮጀክቶቹም በስራ ዕድል ፈጠራና በቴክኖሎጂ ሽግግር ለዜጎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እየበረከቱ ይገኛል ብለዋል::
የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ በበኩላቸው የመጣውን ነዳጅ በአግባቡ በመጠቀም ለታለመለት አላማ ማዋል እንዳለበት ተናግረዉ፣ ባለድርሻ አካላትም ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይከናወን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው ብለዋል።
ወደ ዞኑ ለሚመጡ ሌሎች ባለሀብቶችም መሬት ከመስጠት ጀምሮ መንግስት አስፈለጊውን ድጋፍ በማድረግ እንደሚያበረታታ አቶ ማቴዎስ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፡በየነ ሰላሙ-ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ