ሀዋሳ፡ ሕዳር 14/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 120 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል፡፡
ከተመራቂዎቹ መካከል 67ቱ ወንዶች ሲሆኑ 53 ደግሞ ሴቶች ናቸው።
በምረቃ ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ህዝባችን በቂ የህክምና ይፈልጋል፤ ባልተመቻቸ ሁኔታ ያስተማረንን ህብረተሰብ በቀናነት እና በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ኮሌጁ ከመማር ማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን በሪፈራል ሆስፒታሉ በርካታ ሺህ ለሚቆጠሩ የሲዳማ እና አጎራባች ህዝቦች አግልግሎት እየሰጠ ስለመሆኑ አንስተው አገልግሎቱን ለማጠናከርና ለማስፋፋት እየተሰራን ነው ብለዋል።
የኮሌጁ ኤክስኪዩቲቭ ዳይረክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር አለሙ ጠሚሶ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ለሀገሪቱ ጤና ዘርፉ መጎልበት ያላሳለሰ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል።
ኮሌጁ ባለፉት አመታት ብቻ 2ሺህ 3 መቶ የህክምና ዶክተሮችን በማስተማርና በማሰልጠን ወደ ስራው አለም መቀላቀሉን ጠቅሰዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳና የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሰላማዊ መንገሻ፤ የኢትዮጵያ ህዝብን የጤና ዘርፍ ጥያቄዎችን የመመለስ አዲስ ተመራቂዎች ሀላፊነት አለባችሁ ነው ያሉት።
ተመራቂዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ በአገልጋይነት እና በአመስጋኝነት መንፈስ እንዲያገለግሉም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።