ሀዋሳ፡ ሕዳር 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጌዴኦ ዞን በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተለያዩ ኩነቶች መከበሩን የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ገልጿል።
የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች ክፍሌ የዕለቱን መከበር አስመልክቶ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ይርጋጨፌ ቅርንጫፍ በሰጡት አስተያየት በዞኑ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በዓሉ አንድነትን በሚያጠናክሩና የብሔረሶቦችን የጋራ እሴት በሚገልፁ ኩነቶች መከበሩን አስታውቀዋል፡፡
የዲላ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ሆርዶፋ በበኩላቸው፤ በዓሉ ትውልዱ አንድነትን ከሚሸረሽሩ አስተሳሰቦች በመራቅ በጋራ ማደግ በሚቻልበት መንገድ ስብዕናውን እንዲገነባ ትልቅ ፋይዳ ያለው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዓሉ በዞኑ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በትምህርታዊና አዝናኝ ኩነቶች መከበሩ ተመላክቷል፡፡
ዘጋቢ: ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።