ሀዋሳ፡ ሕዳር 13/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉ የመልማት አቅም ከፍ የሚያደርገውን የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
በሁሉ አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍ የ2017 በጀት አመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትልና የገጠር ተደራሽ መንገድ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምብሶ እንዳሉት የማህበረሰቡ የመልማት ጥያቄ ከሚመልሱ ዘርፎች ዋነኛው የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ነው።
በዚህም የመንግስት ውስን በጀት በመጠቀምና የማህበረሰብ ተሳትፎን በማጎልበት የተሳካ ሁሉን አቀፍ የመንገድ ልማት መከወን እንዲቻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የተደረገ ውይይት ስለመሆኑ አንስተው አሁን ላይ ቢሮው በሶስት የመንገድ ልማት ዘርፎች ላይ አትኩሮ እየሰራ ነው ብለዋል።
እንደ ሃለፊው ገለጻ በክልልሉ በየዩራፕ ስራ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ላለመጠናቀቃቸው ዋነኛ መንስኤ የእዳ ጫና መሆኑን አውስተው የተመደበውን በጀት በአግባቡ በመጠቀም እዳውም እየተከፈለ ፕሮጀክቶቹም መጠናቀቅ አንዲችሉ የአሰራር ስርአት ተዘርግቷል።
የማህበረሰቡን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማሳለጥ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት 10 ተንጠልጣይ ድልድዮችን ለመገንባት ታቅዶ አምስቶቹ በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ያሉት አቶ ማቴዎስ በተለይም በመንግስት በጀት ብቻ የልማት ጉድለቱን ሟሟላት ስለማይቻል ከህበረተሰብ ተሳትፎ እስከ 1 ቢለየን ብር በመሰብሰብ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ ይሰራል ሲሉም ተደምጠዋል።
የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትልና የመሰረተ ልማት ክላስተር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማን ኑረዲን በበኩላቸው በቀመሩ መሰረት የተከፋፈለውን በጀት ለታለመለት አላማ በማዋል ፕሮጀክቶች አጠናቆ ማስመረቅና እዳ መክፈል የበጀት አመቱ ዋነኛ ተግባር መሆኑንና ለውጤታማነቱም ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት።
በዚህ በጀት አስተዳደር ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግም አቶ አማን ኑረዲን ጠቁመው ለዘርፉ ውጤታማነት የህብረተሰብ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የወይይቱ ተሰታፊዎችም የሁሉን አቀፍ የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ የሚመጥን ስራ ከመስራት አኳያ ውስንነት እንዳለ ተናግረው ለዚህ ዋነኛ መንስኤ ደግሞ በጀት መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለይም ተጀምረው ያልተጠናቀቁትን ተደራሽ በመድረግ ላይ ያሉ የድልድይና የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች የሚመጥን የበጀት ቀመር ክፍፍል ሊኖር እንደሚገባም ተሳታፊዎቹ አመላክተዋል።
በመጨረሻም ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች የሚከፋፈለው በጀት በቀመሩ መሰረት በየደረጃው በሚገኙ አካላት ተገምግሞ የጸደቀ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትልና የገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ማቴዎስ ሎምብሶ ናቸው።
ዘጋቢ፣ አማን ቢካ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በጌዴኦ ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች በተለያዩ ኩነቶች ተከበረ
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ባስጀመረው የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ውይይት መካሄድ ጀመረ
የይርጋጨፌ ከተማን የኮሪዴር ልማት ለነዋሪዎች ምቹ ከተማ እንዲትሆን ከማድረግ ባለፈ የከተማዋን ገፅታ የቀየረ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ