እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል አለብን ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ ተናገሩ፡፡
ኢንጂነር አክልሉ በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በከተማና መሠረተ ልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ የውይይት መድረክ እንዳሉት፤ የለውጡ መንግስት መምጣትን ተከትሎ ለሀገሪቱ የምጣኔ ሀብት ዕድገትና ለህዝቡ የጋራ ተጠቃሚነት ፋይዳ ያላቸውን እሳቤዎችን በማምጣት ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡
እነዚህን እሳቤዎች ተከትሎ እንደ ሀገር ያሉንን ሀብቶች በመጠቀም የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ነው ኢንጂነር አክሊሉ ያሳሰቡት፡፡
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዲላ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት ከሌሎች አቻ ከተሞች ጋር እኩል ለማራመድ የተጀመሩ ሥራዎች ቢኖሩም በሚፈለገው ደረጃ ልማቱን ለማፋጠን የህብረተሰቡ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡
በውይይቱም የሀይማኖት አባቶችና የባህል ሽማግሌዎችን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ