ተቋማት ትክክለኛ እና ጥራት ያላቸውን መረጃዎችን በማደራጀት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 12/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለሀገራዊ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ተቋማት ትክክለኛ እና ጥራት ያላቸውን መረጃዎችን በማደራጀት የበኩላቸውን እንዲወጡ የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ጥሪ አቅርቧል።
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር ምክር ቤት ጉባኤና 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ የምክክር አድርጓል።
ወቅታዊ ጋብቻ፣ የፍቺ፣ የልደት እና የሞት ኩነቶች ምዝገባ አተገባበር ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመምከር ያለመ መሆኑም ተመላክቷል።
ተቋማት የዜጎችን ልደት፣ ጋብቻ፣ ሞትና ፍቺ ኩነቶች መረጃ በመመዝገብ እና በማደራጀት ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ የበኩላቸውን እንዲወጡ የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ አሳስበዋል።
ባለድርሻ አካላት በተለይም ጤና፣ ትምህርት፣ ፐብሊክ ሰርቪስ፣ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም ሴቶች ህጻናት ጉዳይ እና የሃይማኖት ተቋማት ዋነኛ ተዋናይ በመሆናቸው ለትክክለኛ መረጃ ጥንቅር የሚሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ከባለድርሻ አካላት አንዱ በሆነው ጤና ተቋም በጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች የተጀመረው የልደት እና ሞት ምዝገባ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጎፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሊቃውንት አዛዜ ገልጸዋል።
በያዝነው ዓመት ከ12ሺህ በላይ ኩነቶችን ለመመዝገብ መታቀዱንና ባለፉት 3 ወራት 1ሺህ 123 የተከናወነ ሲሆን በየኩነት አመዘጋገብ ዙሪያ የህብረተሰቡን አመለካከት ለማሳደግ ሰፊ ስራ እንደሚሰራ የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የወሳኝ ኩነቶች ሥራ ሂደት አሰተባባሪ ወ/ሮ ራድያ ገልጸዋል።
ዘጋቢ – ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ
የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል ዙሪያ የሚተገበሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳሰበ
እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ