የተያዙ ግቦችን በአግባቡ በማከናወን አብዛኞቹ ተግባራት ማሳካት መቻሉን የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታወቀ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የተያዙ ግቦችን በአግባቡ በማከናወን አብዛኞቹ ተግባራት ማሳካት መቻሉን የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስታውቋል።
የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 23ኛ የጋራ ምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተከናውኗል።
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ኸይሩ መሀመድ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ የሚመለከታቸው አካላት አቀናጅቶ በመስራት በአብዛኛው አካባቢ ሰላም ለማስጠበቅ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻሉ ተግባራት ተከናውነዋል።
በየአካባቢው የሚነሱ የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል የክትትል እና የቁጥጥር ስራ ተከናውኗል ብለዋል።
የምናከናውናቸው ተግባራት የጋራ መግባባት በመፍጠር የተሻለ ስራ የሰሩ አካላት ለመለየት እንዲቻል በመስፈርቶች ዙሪያ ወጥ እንዲሆኑ ተደርጓል ሲሉም አቶ ኸይሩ ገልጸዋል።
የምክር ቤቱ የልማት እቅድ ባለሙያ አቶ አዲሱ ክንፈ የ2017 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት የወረዳ እና ከተማ አንዲሁም ቀበሌ ምክር ቤቶች የድጋፍ ሪፖርት እና የ2016 ዓ.ም የወረዳ፣ የከተማና የቀበሌ ምክርቤቶች የምዘና ሪፖርት አቅርበዋል።
የ2016 ዓ.ም የወረዳ፣ የከተማና የቀበሌ ምክር ቤቶች የምዘና ሪፖርት ለምክክር መድረኩ አባላትና ተሳታፊዎች አቅርበዋል።
በየሩብ አመቱ ወረዳና ከተማ ምክር ቤቶች ቀበሌዎች ደግሞ በየወሩ ጉባኤ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም በሪፖርቱ አንስተዋል።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ የወካዮች ምክር ቤት ባለሙያ አቶ አባድር ሀሰን በበኩላቸው፤ በዞኑ ምክር ቤት የሴቶች ተሳትፎ በህግ አውጪ ተቋማት ያላቸው ሚና በተመለከተ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦች ተሰነስተዋል።
በመድረኩ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን የወረዳና ከተማ አስተዳደር አፈጉባኤዎች ይበልጥ በየዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች በየጊዜው መከታተል እንዲቻል ተጨማሪ ስራዎች ከመስጠት ይልቅ መስሪያ ቤታቸው ላይ ማተኮር እንዳለባቸው አንስተዋል።
ከዞን እስከ ወረዳ ብሎም የከተማና የቀበሌ ምክር ቤቶች ለማጠናከር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ በማድረግ እራሳቸውን በአግባቡ እንዲመሩ መደረግ እንዳለበትም ተናግረዋል።
በየጊዜው የሚወርዱ አሰራር እና መመሪያዎች ደንብና ህግጋት፣ አዋጅና ስርአቶች በመረዳት ተግባራዊ ለማድረግ የግንዛቤ ስራዎች በማከናወን እና የሰው ሀይል ቅጥርና ዝውውር እንዲፈቀድም ጠይቀዋል።
ሴቶች በማብቃት በሁሉም ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆኑ ይበልጥ መሰራት እንዳለበትም አውስተዋል።
ምክር ቤቱ እየሰራው ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑንም ተናግረዋል።
የተሻለ አፈፃፀምና ውጤት ያስመዘገቡ የወረዳ የከተማና የቀበሌ ምክርቤቶች እና የዞኑ ምክር ቤት ባለሙያዎች የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዘጋቢ፡ እንዳልካቸው ደሳለኝ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
እርስ በርሳችን ከመቃቃር ይልቅ አንድነታችንን በሚያጠናክሩ ሀሳቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ከተማና ወረዳ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤቶች አሳሰቡ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ገለጹ
ከኑሮ ውድነትና ከኢኮኖሚ ችግር ለመላቀቅ ያሉንን ፀጋዎች በአግባቡ በመጠቀም መስራት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ገለፀ