በልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ የሚመክር ክልል አቀፍ የከተሞች ህዝባዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ ሕዳር 11/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዙሪያ የሚመክር ክልል አቀፍ የከተሞች ህዝባዊ የንቅናቄ መድረክ በጌዴኦ ዞን ገደብ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩ የንቅናቄ መድረኩ ዋና ዓላማ በሀገር ልማት ዕድገት ውስጥ የከተማና ከተሜነት ድርሻን ማሳደግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የከተሞችን የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ ውይይቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን የከተማው ከንቲባ አቶ ታሪኩ ሮቤ አስረድተዋል፡፡
በንቅናቄ መድረኩ ከከተማ ቀበሌያት የተወጣጡ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የሀይማኖች አባቶች፣ የባህል ሽማግለዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።