የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ለ3ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸው ተገለጸ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለ3ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔረሰቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር የተለያዩ የዝግጅት ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
ለበዓሉ ድምቀት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የገለፁት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ፥ በዓሉ በክልሉ ሁሉም አከባቢዎች ከቀበሌ ጀምሮ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ቦታዎች በድምቀት እየተከበረ መቆየቱን አስረድተዋል።
አፈ-ጉባኤው አክለውም፥ የብሔረሰቦች ቀን በዓል በክልሉ ያሉ 13 ብሔረሰቦች የየራሳቸውን ቱባ ባህል ለሌላው የሚያስተዋውቁበት ትልቅ መድረክ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የበዓሉ አከባበር ይዘት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደመጣ ያስረድት አፈ-ጉባኤው በዓሉ የብሔሮችን የእርስበርስ ግንኙነት እንደሚያጠናክር አስረድተዋል።
በዘንድሮ የብሔረሰቦች ቀን በዓል የክልሉን ቱባ ባህልና የተለያዩ ወጎችን ከወትሮ በተለየ መልኩ ለማስተዋወቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ አብራርተዋል።
ለበዓሉ ዝግጅት ከክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ገልጸው፥ በየደረጃው የተቋቋመው ኮሚቴዎች በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
በዓሉ ለክልሉ ገፅታ ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ የገለፁት አፈ ጉባኤው፥ በህዳር 29/2017 በአርባምንጭ ከተማ በሚካሄደው አገር አቀፍ መድረክ ላይ በተደራጀ ሁኔታ ተሳትፎ ይደረጋል ብለዋል።
ለበዓሉ ስኬታማነት በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ተላልፏል።
ዘጋቢ: ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች