የወላይታ ዞን ግብርና መምሪያ ወቅታዊ የግብርና ልማት ተግባራት ላይ ያተኮረ ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ አካሄደ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም በንቅናቄው መድረክ ባስተላለፉት መልዕክት በግብርናው በሁሉም ዘረፍ የምርታማነት እምርታ ከፍ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ ጠቁመዋል።
አክለው ለግብርናው ምርታማነት በቴክኖሎጂና በግብአት አጠቃቀም የተሻለ ለማድረግ ይሠራል ብለዋል።
በየወቅቱ የሚሠሩ የግብርና ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ በየዘርፉ ያለው ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
የዞኑ የግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዳንኤል ደሌ እንደተናገሩት የግብርና ሥራዎችን በዘመናዊ መንገድ በማምረት ምርታማነት ለማሳደግ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያሻ ጠቁመዋል።
በቀለች ጌቾ – ከዋካ ቅርንጫፍ
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!