ምክር ቤቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክረው ሊያስቀጥሉ ይገባል – አቶ ወንድሙ ኩርታ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልል እና ዞኖች የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉአላዊነት የሚረጋገጥባቸው እንዲሆኑ ለማስቻል በየደረጃ ባሉ መዋቅሮች ኃላፊነታቸውን በተገቢው መወጣት ይገባቸውል ብለዋል።
በ2017 በጀት ዓመት ከታቀዱት ውስጥ በ1ኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ መልካም ተግባራትን ማስቀጠልና በክፍተቶች ላይም ቀጣይ በትኩረት በመስራት የህዝብ ተጠቃሚነትን በሚሳድጉ ተግባራት ላይ ትኩረት ሊሠጥ እንደሚገባም ተናግረዋል።
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፌ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ዳርጫ በበኩላቸው በተለይ የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮች ለአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ የሚያስችል ትልቅ መድረክ ስለሆነ ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ልሰጥ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የክልሉ እና የየዞኖች የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዚህም በዞኖች ደረጃ የምክር ቤት ጉባኤ በታቀደው ልክ የተካሄደ መሆኑና በተደረጉ ጉባዔዎችም በተለያዩ አጀንዳዎች አባላት ተወያይተው ውሳኔ ያሳለፉበት እንደሆነ ተመልክቷል።
የክልሉን ምክር ቤት ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ሀብታሙ መንግስቱ በመንግስት አስፈፃሚ አካላት የተሰሩ የዕቅድና አፈጻጸም ሪፖርቶች በምክር ቤቶች የተገመገሙበትና በቀረቡ በተለያዩ ሹመቶች ዙሪያም ጉባኤው የገመገመበት አፈፃፀምም የተሻለ መሆኑ አብራርተዋል።
የመንግስት አካላት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተገቢው በመወጣት የልማት ፣ ዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ተግባራትን ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ሰለመስራታቸው ክትትልን ቁጥጥር መደረጉም ተገልጿል።
የበጎ ተግባራትን ለማሳደግ ለሁለት አረጋዊያን የመኖሪያ ቤት በካፋ እና ኮንታ ዞኖች በክልሉ ምክር ቤት የተገነባላቸው እንደሆነም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ምክር ቤቶች የህዝብ ሉኣላዊነት መገለጫ እንደመሆናቸው በህዝብ ዘንድ እንደችግር የሚነሱ ጉዳዮችን ለማረም የተጠናከረ ስራ እንደሚጠበቅ በመድረኩ ተገልጿል።
በአፈፃፀሙ የታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰሩ የተናገሩት የመድረኩ ተሳታፊዎች በኦዲት የሚገኙ ጉድለቶችን በሚመለከት የፍትህ አካላት ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ የጋራ መድረክ ተፈጥሮ በመናበብ ህዝብ የሚያነሳቸው ችግሮች እንዲፈቱ ማስቻል ይገባል ብለዋል።
እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ለህዝብ እንዲደርሱ ከማስቻል ረገድ ሚዲያ ተቋማትን እየተጠቀሙ መሆናቸውን አንስተው የዋካ ኤፍ ኤም ጣቢያ በታርጫ አለመደመጡ ችግር ደግሞ እንዲፈታ ጠይቀዋል።
በመድረኩ የክልሉ ዋናና ምክትል አፈጉባኤዎች፣ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የ6ቱም ዞኖች አፈጉባኤዎች፣ የልማት ዕቅድ ባለሙያዎችና ቋሚ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ: ዮሐንስ መካሻ – ከዋካ ቅርንጫፋችን
More Stories
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ
የትምህርት ጥራትና ውጤት መሻሻል ዙሪያ የሚተገበሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳሰበ
እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ