ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ተጓዦች አቀባበል ለማድረግ ተዘጋጅተናል- የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ
በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓልን በድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል።
የዓሉን አከባበር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሀዋሳ ከተማ ውይይት ተደርጓል።
የክልሉ የምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ በዚህ ወቅት እንደገለፁት በዓሉ አንድነት እና ህብረ ብሄራዊነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር የክልሉ መንግሥት ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።
የበዓሉ አክባሪዎች የሲዳማ ክልልን በማቋረጥ ስያልፉ በመግብያና መተላለፊያ አከባቢዎች ለእንግዶች የሲዳማን ህዝብ እሴት በሚገልጽ መልኩ ደማቅ አቀባበል ይደረጋል ። ይሄን ተግባር ለማሳለጥም ሰባት ወረዳዎች እና ሶስት ዞኖች መዘጋጀታቸውም ተመልክቷል ።የተጓዦችን ደህንነት ለመጠበቅም የፀጥታ አካላትና ህብረተሰቡ በጋራ ይሰራሉ ።
በዓሉን በክልሉ በሁሉም ዞኖች ወረዳዎች በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጀት ተደርጓል ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ የበጎ አድራጎት ስራዎች፣ የደም ልገሳ እና በስፖርታዊ ውድድሮች ዋና ዋና ተግባራት ናቸው።
የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሐሳብ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ይከበራል።
ዘጋቢ፡ ጀማል የሱፍ

More Stories
ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ፣ የዕጩ ማስተዋወቂያ እንዲሁም የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ አካሄደ
ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ጥራት ያለው የአይን ህክምና በሀገሪቱ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ
ብልጽግና ፓርቲ የማህበረሰቡ ችግር የሚቀርፉ ፕሮጀክቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ በውጤታማነት ለአገልግሎት እያበቃ ነው – ዶ/ር መሀመድ ኑርዬ