በባስኬቶ ዞን የላስካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት በከተማው ፀጥታ ዙሪያ ከነጋዴ ማህበረሰብ ጋር መክሯል።
የከተማ ፀጥታ ሁኔታና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና በሚል በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ የላስካ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዷለም ምህረቴ፤ ከተማው የሶስት መዋቅሮች መቀመጫ እንደመሆኑ መጠን በከተማው የሚመጡ እንግዶችና የከተማ ነዋሪዎች በሠላም ወጥተው እንዲገቡና ነጋዴው ማህበረሰብ ንግዳቸውን በአግባቡ እንዲያንቀሳቅሱ ሠላም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው በሠላም ዙሪያ ተቀናጅተን ለመስራት የታሰብ መድረክ ነው ብለዋል።
የላስካ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር አዳኝ አማሬ በበኩላቸው፤ የሠላም ጉዳይ የማይመለከተው አካል ባለመኖሩ በከተማችን የፀጥታ ነባራዊ ሁኔታ ላይ ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር ተቀናጅተን መስራት ሚናው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች አቶ ሰይድ ጉዳዶ እና ነፃነት ገዛኸኝ በጋራ በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ በፊት የፀጥታው መዋቅር በዚህ መልኩ ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር በግልጽ የሚወያይበት ሁኔታ እንዳልነበረ ገልጸው አሁን የተጀመረውን ጥረት አድንቀው ተጠናክሮ እንቀጥል አሳስበዋል።
ከዚህ በፊት ህገ ወጥ ስራዎች፣ የስርቆትና የንብረት ዘረፋዎችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ያለመስራ ችግሮች እንደነበሩ አንስተው አሁን እየተሰራ ባለው የሪፎርም ስራ ለውጥ መኖሩን ገልፀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ሠላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዷለም ምህረቴ በውይይቱ ለተነሱ ጉዳዮች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ትላንት ያለፍንበት ነዋሪዎችን ያስቆጣበት ሁኔታ በማሻሻል አሁን የተገኘውን ሠላም በማጠናከር ለነገ ዘላቂ ሠላም ተቀናጅተን መስራት ወሳኝ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ አብርሃም ኩምሳ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የልማት፣ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ሂደት ለማፋጠን ድርሻው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሻሻልና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተደራሽነቱን ለማስፋት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።