የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ለባለሙያዎች የዲጂታል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወሳኝ ኩነቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደነቀ እንደገለፁት የኩነቶች ምዝገባ የሶሺዮ ኢኮኖሚክ ዳታ ለመያዝና ዲጂታል ቴክኖሎጂን ለመተግበር ክፍተኛ ሚና አለው።
ይህም በሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ሲደረግ ለሀገሪቱ ብሎም እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አቶ ስለሞን ተናግረዋል።
የዳውሮ ዞን ሠላምና እና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ዳንኤል ሄሎሬ ኩነቶች በአግባቡ እና
በዘመናዊ መንገድ መመዝገብ አሰፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል።
መንግስት ፍትሃዊ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ዘመናዊ የመረጃ ቅብብሎሽ ከፍተኛ ፋይዳ እንዲኖር ያደርጋል ብልዋል።
ወሳኝ ኩነት መረጃ ለማስመዝገብ በቀበሌ ደረጃ ግንዛቤ በመፍጠር የኩነቶች ምዝገባ በህብረተሰቡ ዘንድ በመልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያደርጋል ብልዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃ ቅበላ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በረከት መላኩ፤ ኩነቶች ለግለሰቦች እንደማስረጃ ሊቀርብ የሚችሉ እንደሆነ ተናግረዋል።
ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ምዝገባ ባለቤት በመሆን ከአካባቢው ሳይርቅ መመዝገብ እንዳለበት ተናግረዋል።
በተጨማሪም የኩነቶች ምዝገባ ማስፋፋት ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ለማጠናከር እንዲቻል ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በትኩረት መተግበር እንዳለበት አሳሰበዋል።
ሥልጠናው ለ10 ወረዳዎች፣ ለ2ቱ ከተማ አስተዳደር መዋቅር ፎካሎችና ከቀበሌ ለተውጣጡ ሥራ አስኪያጆች በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሂደት ዙሪያ የአቅም ግንባታ ተሰጥቷል።
ይህም በቀጣይ ለተግባራዊነት አቅም እንደሚስጣቸው ተጠቁሟል።
ዘጋቢ: አንዱዓለም ኡማ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሻሻልና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተደራሽነቱን ለማስፋት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።