የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክልሉ ተመስርቶ ወደ ስራ ከገባ በኋላ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ መምጣቱን የፍርድ ቤቱ ተገልጋዮች ተናግረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ በክልሉ ለሚገኙ ተገልጋዮች በቅርበት ሆኖ ቀልጣፋ የፍትሕ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት ተገልጋዮቹ ተናግረዋል።
ተገልጋዮቹ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተለይ አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማገዝ ተደራሽነቱን ይበልጥ ማስፋፋት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቆጭቶ ገብረማርያም፤ ክልሉ ሲደራጅ በፍትህ ስርአቱ ውስጥ የነበሩትን የህብረተሰቡ ችግሮች በጥናት በመለየት ወደስራ የተገባ ሲሆን ይህም ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን ማድረጉን ተናግረዋል።
ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ ግባቸው ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በክልሉ የፍትህ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከቴክኖሎጂ ጋር ተያይዞ የሚታዩትን ችግሮች ለመፍታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ፍርድ ቤቱ አሁን ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ለማሻሻል እንዲችል ብቃት ያለው የሰው ሀይል ከማሟላት ባሻገር በተቋሙ መዋቅራዊ ማሻሻያዎች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የክልሉ መንግስት ከምን ጊዜም በላይ ህዝቡን ለማገልገል ዝግጁ ነው -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
የጎፋ ዞን ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር መርሃ-ግብር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል
ከ19ሺህ በላይ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው ወደ ተግባር መግባታቸውን ተገለጸ