በባስኬቶ ዞን ላስካ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማትና እውቅና አበረከተ
በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የላስካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር አንለይ ወንዲፍራው፤ ተማሪዎች ላመጡት ውጤት ዕውቅና መስጠትና ማበረታት በሚሄዱበት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡና አካባቢያቸውን እንዲያስጠሩ ከማገዙም ባሻገር ለሌሎች ተማሪዎች መነቃቃትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ትምህርት ለሀገር ዕድገት ጉልህ ድርሻ ከሚያበረክቱ ተቋማት ዋነኛው መሆኑን ያመላከቱት ከንቲባው፤ በዘርፉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀው ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከፍተኛውን ድርሻ ለተወጡ መምህራንና ለተማሪ ወላጆች ምስጋና አቅርበዋል።
የላስካ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አወል ገዛኸኝ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን ከላስካ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 5 ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመግቢያ ውጤት እንዳስመዘገቡ ገልፀዋል።
በትምህርት ቤቱ ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ተማሪ አንተነህ አለማየሁ በተፈጥሮ ሳይንስ 426፣ ተማሪ በረከት በቀለ በማህበራዊ ሳይንስ 351 በማስመዝገብ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
ለስኬቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት የትምህርት ቤቱ መምህራን በበኩላቸው፤ ተማሪዎች በሚማሩበት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ከቀድሞው ይበልጥ እንዲተጉ ምክረ ሀሳብ ሰጥተው ወደ ከፍተኛ ትምህር ለሚሄዱት መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።
ሽልማቱ የተበረከተላቸው ተማሪዎች ልምዳቸውንና ተሞክሯቸውን ለሌሎች አጋርተው በቆይታቸው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
ዘጋቢ፡ አብርሃም ኩምሳ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ
ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የልማት፣ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ሂደት ለማፋጠን ድርሻው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ