በምክክር መድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ፣ የብሄረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ገመቹ አረቦ፣ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ባዩሽ ተስፋ፣ የዞን እና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
የመክፈቻው ንግግር ያደረጉት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፤ የመድረኩ ዓላማ የህዝቦችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና ተደራሽነትን በማረጋገጥ እኩል ተጠቃሚነት ለማስፈን እንደሆነ ተናግረዋል።
ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሳይረጋገጥ ጠንካራ ሀገረ-መንግስት መገንባት አዳጋች ነው ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው፤ ከድጎማ በጀት ግልፀኝነት እንዲሁም ከአሳታፊነት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶችን መቅረፍ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ለውይይት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ሄኖስ ካሳ – ከሆሳዕና ጣቢያችን
More Stories
እምቅ ሀገራዊ ሀብቶቻችን በተሻጋሪ እሳቢያችን በማልማት እንደ ሀገር የተጀመረውን የዕድገት ጉዞ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ
ተቋማት ትክክለኛ እና ጥራት ያላቸውን መረጃዎችን በማደራጀት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
የ40 ዓመታትን ቂም በቀል የሻረው የጎፋዎች የእርቅ ማዕድ የ”ባራንቼ ዎጋ” ስርዓት