የፊታችን ቅዳሜ በይፋ የሚመሰረተው ይኸው የዋካ ከተማ አስተዳደር፤ የዘመናት የህብረተሰቡ ጥያቄ ሆኖ የቆየ ሲሆን ጥያቄው አሁን ምላሽ በማግኘቱ መርካታቸውን ነዋሪዎቿ ተናግረዋል።
ከተማዋ እንደቀደምትነቷ ያለማደጓን አክለው የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ከተማዋን ካለችበት ደረጃ ከፍ በማድረግ ለማልማት እየተደረገ ያለውን ጥረት በእውቀት፣ በገንዘብና በጉልበት ለመደገፍ ቁርጠኞች ስለመሆናቸውም አረጋግጠዋል።
ምስረታውን ተንተርሶ ወደ ከተማዋ የሚመጡት እንግዶችን ለመቀበል ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ አሸናፊ ግዘው – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የሆሳዕና እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከአንድ መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!