የትራፊክ አደጋን ለመከላከል በህብረተሰቡ ዘንድ በጎ ተፅእኖን መፍጠር ከሚችሉ ግለሰቦች ጋር የሚሠሩ ሥራዎች የሚበረታቱ እንደሆነ ተገለፀ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 03/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትራፊክ አደጋን ለመከላከል በህብረተሰቡ ዘንድ በጎ ተፅእኖን መፍጠር ከሚችሉ ግለሰቦች ጋር የሚሠሩ ሥራዎች የሚበረታቱ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ ገዳይነቱና ጎጂነቱ እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ እንዲሁም ስለ መንገድ ደህንነት ግንዛቤን ለመጨመር የሚረዱ ተግባራት በጌዴኦ ዞን የተለያዩ ከተሞች ላይ ተከናውነዋል፡፡
የዲላ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪ ኢንስፔክተር ሀብታሙ ህርባዬ እንደተናገሩት፤ በዲላ ከተማ ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር ስለ ትራፊክ አደጋ ግንዛቤ ለመፍጠር የተደረገው ተግባር በሚገባ የሚያግዝ ነው፡፡
ታዋቂ ግለሰቦች ስለ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት ለማህበረሰቡ ለማስገንዘብ ስላደረጉት ትብብርም ከልባቸው አመስግነዋል፡፡
ከዋና ሥራው ባሻገር በበጎ ተግባሩና በሰብዓዊ ሥራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልካም ተፅእኖን መፍጠር የቻለው የይርጋጨፌ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ አባል ሳጅን መልካሙ በየነ እንደተናገሩት፤ ታዋቂ ግለሰቦች ሥራዬን ለማገዝ ብለው ይርጋጨፌ ከተማ ላይ መገኘታቸው ለሥራዬ ተጨማሪ ሞራል ሆኖኛል፡፡
የገደብ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ዳዊት ደግፌ በበኩላቸው፤ ዋናው መንገድ ከተማውን ለሁለት አቋርጦ የሚያልፍ በመሆኑና ከተማው በርካታ የሁለት እግር ሞተር ሳይክል የሚገኝበት እንደመሆኑ መሠል ሥራዎች አደጋውን ለመቀነስ አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
አደራጅ ዘሪሁን ማስታወቂያና መድረክ ሥራ ከጌዴኦ ዞን አስተዳደርና ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ በርካታ አርቲስቶችና የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ተሳትፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አብነት አበበ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
የዲላ ከተማን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን በትኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ
በክልሉ ያሉ የገቢ አማራጮችን በተገቢው አሟጦ ከመሰብሰብ አንፃር ያሉ ውስንነቶች ማረም እንደሚገባ ተገለፀ
ቡናና ሻይ ቅመማቅመም ምርቶችን አብዝተዉ በማምረት ኢኮኖሚያቸዉን እያሳደጉ መሆናቸዉን በዳዉሮ ዞን ድሳ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ