በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ሊበን ዞን 2 ሺህ ኪሎ ዋት ኃይል ማመንጨት የሚችል የቦቆሎማዮ ከተማ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ
የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ ከ60 ሺህ በላይ ህዝብ የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ነው ተብሏል።
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግንባታና ዝርጋታም ከ800 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት ተመላክቷል።
በሶማሌ ክልል ከተገነቡት የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች መካከል የቦቆሎማዮ ፕሮጀክት 4ኛው ሲሆን በግዝፈቱ በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ እንደሆነም ተገልጿል።
አሁን ላይ ከ21 ኪሎ ሜትር በላይ የመስመር ዝርጋታና የ5 ትራንስፎርመር ተከለ ተጠናቅቋል።
በፕሮጀክቱ 8 ሺህ የቆጣሪ ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከቦቆሎማዮ ከተማ በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኙ የስደተኞች ማረፊያ ካምፖችንም ጭምር የመብራት ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።
ከለውጡ ወዲህ በሱማሌ ክልል ያሉ 81 አዳዲስ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አስታውቀዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ለይ የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ እንዲሁም የሶማሌ ክልል ሀገር ሽማግሌዎች እና የቦቆሎማዮ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ጌታሁን አንጭሶ

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።