ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበረው በዓል አንድነትንና ወንድማማችነትን እንደሚያጠናክር የዞኑ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
የአሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ስመኝ ተስፋዬ እንደገለፁት፤ ለ19ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ “ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጸው፤ እንደዞን በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የኣሪ ብሔር ዘመን መለወጫ ድሽታጊና በሚከበርበት ዋዘማ መሆኑ ለየት ያደርገዋል ያሉት አፌጉባኤዋ፤ ቀበሌያት ከህዳር 5 ጀምሮ ሲያከብሩ ህዳር 15 ዞናዊ የብሔረሰቦች በዓል እንደሚከበረም አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦች ከሚያለያዩ ነገሮች በላይ አንድ የሚያደርጉ በርካታ ጉዳዮች እንዳሉን ለዓለም የምናሳይበት መድረክ መሆኑን የሚገልፁት የዞኑ ነዋሪዎች፤ ለበዓሉ ድምቀት የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይም በዓሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት የሚከበር በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀው በጋራ ጉዳይ በመሰባሰብ ባህላዊ እሴቶችን ለማሳደግ እጅ ለእጅ የምንያያዝበትና ቃልኪዳናችንን የምናድሰበት መድረክ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በከተሞች የሚስተዋሉትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡ ሰፊ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ
ማህበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመምራት እና በመጠቀም የአካባቢን ገጽታ መገንባት እንደሚገባ ተጠቆመ
የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መስፋፋት ጥራት ያለው ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ