የትምህርት ማጣቀሻ መጽሐፍት፣ ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ታብሌቶች፣ ለትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ማብሰያዎች፣ ለዘርፉ ሥራ ክትትል ምቹ ሁኔታን የሚፈጥሩ ሁለት እግር ሞተር ሳይክሎች በድጋፍ መልክ ከተበረከቱ ቁሳቁሶች መካከል ይጠቀሳሉ።
በድጋፍ መርሐ ግብሩ የተገኙት የኢፌዲሪ የቀድሞ ቀዳማዊት እመቤት እና የኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ እንደገለፁት፤ በደቡብ ኦሞ ዞን ያሉ ማህበረሰቦች ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ተላቀው ማየት የሚል ራዕይ አላቸው።
ፋውንዴሽኑ በዞኑ በጤና፣ በተማሪዎች ምገባ፣ በሴቶችና ወጣቶች ኢኮኖሚ አቅም ግንባታና ስራ ዕድል ፈጠራ እየሠራ መሆኑን ያብራሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ፤ ጠንክረንና ተቀናጅተን ከሠራን የማይለወጥ ነገር እንደሌለ ለማየት በቅተናል ብለዋል።
ድጋፍ የተደረገውና በቀጣይ በዞኑ አራት ወረዳዎች ማለትም በናፀማይ፣ ሐመር፣ ዳሰነችና ኛንጋቶም ወረዳዎች ለሦስት ዓመታት የሚተገበር የግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ የምግብ እና ስነ-ምግብ ዋስትና በቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ የኃይለማሪያም እና ሮማን ፋውንዴሽንና ባለድርሻ አካላት ጋር የሚተገብር ፕሮጀክት አካል ነው ሲሉ ወ/ሮ ሮማን አስረድተዋል።
ፋውንዴሽኑ በዞኑ የዜጎች በተለይም የአርብቶ አደር ልጆች በትምህርት ልማት በስፋት እንዲሳተፉ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን የገለፁት የደቡብ ኦሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ ታደለ ጋያ ናቸው።
በዚህም ተጨባጭ ለውጥ ማየት መቻሉን የተናገሩት አቶ ታደለ፤ መንግስት እየሠራ ካለው ልማት በተጨማሪ የልማት አጋር አካላት ሚና የጎላ ነው ብለው ለፋውንዴሽኑ ምስጋና አቅርበዋል።
በየአካባቢው ኋላ ቀር የሆኑ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስቀረት ግዴታ መሆኑን በመውሰድ፤ የሴት ልጆች ትምህርትን ጨምሮ ኢኮኖሚያዊ ጫናን ለማስቀረት የመንግስት አመራር በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በመድረኩ የተገኙ አካላትም ለአካባቢው ሁሉ አቀፍ ለውጥ ከፋውንዴሽኑ ጋር በትብብር እንደሚሠሩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ዘጋቢ: ተመስገን አበራ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ጤና ጣቢያው እየሰጠ ባለው አገልግሎት መደሰታቸውን ተገልጋዮች ተናገሩ
የሰላምና የመከባበር ባህልን ለማስቀጠል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ
የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል እንደሚገባ ተገለጸ