የአራቱም ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም እና አጠቃላይ ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ የሚገመግም የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

የአራቱም ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም እና አጠቃላይ ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ የሚገመግም የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

ሐዋሳ፣ ጥቅምት 27/02/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አፈጻጸምና አጠቃላይ ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ የሚገመግም የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በቀድሞው የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ተቋቁመው የነበሩ እና አራቱም ክልሎች ሲደራጁ የጋራ ሃብት ሆነው እንዲቀጥሉ የተወሰኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ማለትም የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት፣ የደቡብ ካፒታል አክስዮን ማህበር፣ የኦሞ ባንክ እንዲሁም ሴራዴፍ ኮርፖሬት አፈጻጸም ግምገማ የየክልሎቹ ርዕሰ መስተዳድራን፣ የልማት ድርጅቶቹ የስራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው የውይይት መድረኩ እየተካሄደ ያለው፡፡

በውይይት መድረኩ የልማት ድርጅቶቹ በአፈጻጸም ያስመዘገቧቸውን ውጤቶች እና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በመገምገም እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የጋራ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡