የአራቱም ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ
የልማት ድርጅቶቹ በቀጣይ ጠንካራና ተወዳዳሪ ተቋማት ሆነው እንዲቀጥሉ የክልሎቹ መንግስታት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት፣ የደቡብ ካፒታል አክስዮን ማህበር፣ የኦሞ ባንክ እንዲሁም ሴራዴፍ ኮርፖሬት በቀድሞ የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ተቋቁመው የነበሩ እና አራቱም ክልሎች ሲደራጁ የጋራ ሃብት ሆነው እንዲቀጥሉ የተወሰኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ የሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የጋራ ሃብት የሆኑት የልማት ድርጅቶች አፈጻጸም እና አጠቃላይ ተቋማቱ ያሉበትን ደረጃ የየክልሎቹ ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የየተቋማቱ ኃላፊዎች የአፈፃጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የልማት ድርጅቶቹ በበጀት ዓመቱ በጥንካሬ ያከናወኗቸውን ተግባራት አጠናክረው በመቀጠል ጠንካራና ተወዳዳሪ ተቋማት ሆነው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሮቹ ገልጸዋል፡፡
የልማት ድርጅቶቹ የ4ቱ ክልሎች የጋራ ተቋማት በመሆናቸው በአፈጻጸም ወቅት ለገጠሟቸው ተግዳሮቶች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት እንደሚሰሩም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በቀጣይ ትኩረት በሚሹ እና ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን ተከታታይነት ያለው የጋራ የውይይት መድረክ እንደሚፈጠርም ተመላክቷል፡፡
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ