የምግብ ዋስትና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በጥምረት እየተሰራ ነው – የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ
ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የምግብ ዋስትና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑን የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።
ዞናዊ የበጋ መስኖ ወቅታዊ ስራዎች ማስፈጸሚያ የፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ ተካሂዷል።
በዞኑ መዋቅሮች የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች የስራ ውጤታማነትን መከታተል እንደሚገባም በመድረኩ ተመልክቷል።
የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አባይህ አበራ በበጋ መስኖ ንቅናቄ መድረክ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፤ ሀገራዊ የሌማት ትሩፋት የተጀመረበት ዞን መሆኑን አንስተው አፈፃጸሙ ለውጥ እንዲያመጣ አቅዶ መስራት ያሻል ነው ያሉት።
ዞኑ ካለው ጸጋ ረገድ ከክልሉ አልፎ ሀገርን መመገብ ይችላል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው 2017 በጋ መስኖ የበለጠ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያሰስፈልግ ጠቁመዋል።
የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ማጌሶ ማሾሌ እንደተናገሩት፤ ግብርናው የኢኮኖሚ ዋልታ ሆኖ በተግባር በተገለጸበት ወቅት ስለምንገኝ ለዘርፉ ልማት እንሰራለን።
በ2017 ምርት ዘመን በግብርና ምርት እድገት ላይ እምርታ ለማስመዝገብ ገበያን መሰረት ያደረጉ የመስኖ ልማትን ለማጠናከር ግብ ተጥሏልም ነው ያሉት።
ባለፈው የምርት ወቅት በበጋ መስኖ ልማት የተስተዋሉ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር እንደነበር ያወሱት አቶ ማጌሶ ዘንድሮ ከ55 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በማልማት በሁሉም ሰብሎች ከ20 ሚሊየን 814 ሺህ 827 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ጠቁመው በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በሄክታር 34 ኩንታል ለማድረስ ግብ ተጥሏል ብለዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ውጤት እንዲያመጡ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር አጣምሮ መምራት የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል።
ቡና እና ቅመማቅመም ዘርፍ ዞኑ የክልሉን 9 በመቶ ይሸፍናል ያሉት አቶ ማጌሶ ከ22 ሺህ 622 ሄክታር 105 ቶን ቡና የተሰበሰበ ቢሆንም ለማእከል የቀረበ ቡና አለመኖሩን በመጠቆም ቀጣይ በዘርፉ ሰፊ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ አፈጻጸሙ ያሳያል ብለዋል።
በመድረኩ ከተሳተፉት መካከል የአርባምንጭ እጸዋት ክሊኒክ ኃላፊ አቶ ሙላለም መርሻ እንደተናገሩት፤ የማንጎ በሽታን ለመከላከል አበረታች ውጤት ተገኝቷል።
ለፍራፍሬ ምርታማነት ችግር የማሳ እንክብካቤ እጥረት ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።
ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ግብርና ኮሌጅ የተገኙት ዶ/ር ደግፌ አሰፋ እንደጠቆሙት፤ አርሶ አደሩ በግብርና ባለሙያው እየተደገፈ እንዳልሆነ አንስተው ከበሽታ የጸዳ እንሰት ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት እየተሰራ ነው።
በሽታን የሚቋቋም የበቆሎ ዝርያ በስፋት ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑን አስረድተዋል።
በንቅናቄ መድረኩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ ከፍተኛ የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ አሰግድ ተረፈ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
በኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን አዘጋጅነት በደቡብ ኦሞ ዞን ያሉ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ውይይት በቱርሚ ከተማ እየተካሄደ ነው
ወጥ የሆነ ሀገራዊ አንድነትና እሳቤ ኖሮን ህዝቡን አቀናጅተን እንድንመራ የሚያስችል ስልጠና አግኝተናል ሲሉ በኣሪ ዞን 3ኛ ዙር የመካከለኛ ሰልጠኝ አመራሮች ገለፁ
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለሀገራዊ ዕድገት የሚኖረው ፋይዳ የጎላ በመሆኑ ተቋማት ትክክለኛ እና ጥራት ያላቸውን መረጃዎችን በማደራጀት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ተጠየቀ