ሀዋሳ፡ ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በገጠርና በከተማ ኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩት ባለሃብቶች ኢንቨስት አድርገው እንደሚጠቀሙ ሁሉ ህዝብንና መንግስትን መጥቀም እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡
በኮንታ ዞን አመያ ከተማ የኢንቨስትመነት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ግብረ መልስና የዕውቅና ፕሮግራም መድረክ ተካሂዷል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የግሉ ሴክቴር ትልቅ ድርሻ ያለው በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
በገጠርና በከተማ ኢንቨስትመንት ሥራ ላይ የተሰማሩት ባለሃብቶች ኢንቨስት አድርገው እንደሚጠቀሙት ሁሉ ህዝብንና መንግስትን መጥቀም እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የኢኮኖሚ ዕድገት ለማሳለጥና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ኢንቨስትመንት ማስፋፋት አብይ ተግባር በመሆኑ በተወዳዳሪነት፣ በስራ ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂና ክህሎት ሽግግር ሚናው እየጎላ መምጣቱን የዞኑ ንግድ፣ ገበያ ልማትና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ኡቴ ተናግረዋል።
ይሁን እንጅ ተሳታፊ ባለሃብቶች መንግስት የፈጠረውን ምቹ የኢንቨሰትመንት አጋጣሚን በመጠቀም ከፍተኛ መዋዕለ ነዋያቸውን እያፈሰሱ ቢገኙም ልማቱ በሚፈለገው ልክ ባለመሰራቱ የተሻለ ውጤት ማየት እንዳልተቻለ ነው የጠቆሙት።
በዞኑ በገጠርና በከተማ በኢንቨስትመንት የተሰማሩት ባለሃብቶች ለወጣቶች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል የፈጠሩ ቢሆንም አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ነውም ተብሏል።
የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በገጠር የግብርና ኢንቨስትመንቶች ላይ እንቅፋት በመሆኑ በሙሉ አቅም ለማልማት እንዳልተቻለም ሀሳብ ተነስቶ ውይይት ተደርጓል።
ከማዕድን ዘርፍ ጋር ተያይዞ የአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
የከተማ ኢንቨስትመንቶች ከባንክ ጋር የማስተሳሰር ስራ በሰፊው እንዲሰራ ባለሃብቶች ጠይቀዋል።
የተነሱ ዋና ዋና ችግሮችን በመቀናጀት እንደሚሰራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከስምምነት ተደርሷል።
በመጨረሻም የተሻለ አፈፃፀም ላላቸውን ኢንቨስተሮች ዕውቅና ተሰጥቷል።
ዘጋቢ፡ አብዮት እሸቱ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
የሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በስፖርትና ባህል ልማት ዘርፍ የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ አበክሮ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
ህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም አደመጠ
ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሠራ የዲላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ