ሀዋሳ፡ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በ32 ፕሮግራሞች የታቀፉ 64 ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 4.3 ቢሊየን ብር የተለያዩ የልማት ስራዎች እያከናወኑ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ።
የክልሉን እምቅ አቅሞችን ወደ ተጨባጭ ሀብት በመቀየር የህዝቦችን አንገብጋቢ መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎችን ባልተራዘመ ጊዜ ደረጃ በደረጃ አየመለሰ ሊሄድ ይችል ዘንድ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅቶች ሚና ከፍያለ ቢሆንም እንደ ክልል የመልማት አቅም እና የልማት ክፍተቶች አንጻር ሲታይ በርካታ ስራን የሚፈልግ መሆኑን ነው የክልሉ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ የተናገሩት።
በክልሉ እየሰሩ ያሉት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ሚናም ቀላል የሚባል እንዳልሆነና ከሚተገብሩት ተግባር አንጻርም ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።
በክልሉ በ32 ፕሮግራሞች የታቀፉ 64 የሲቭል ማህበራት ፕሮጀክቶች መኖራቸውን የተናገሩት ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በዚህም 4.3 ቢሊየን ብር በጀት መድበው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በየአመቱ እስከ 1 ቢሊየን ብር በጀት በማፍሰስ የኢኮኖሚ ተዋናይ ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተለይም በጤናው ዘርፍ፣ በቤተሰብ ምጣኔ፣ በተቋማት ግንባታና ኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ እየሰሩ ሲገኙ በግብርናውም ዘርፍ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሰብል ምርት፣ በፍራፍሬ ልማትና በንብ ማነብ በህብረት ስራ ማህበራት እየሰሩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በትምህርት ዘርፍም ቢሆን በመደበኛ የትምህርት ስራዎች በትምህርት ቤት ግንባታዎች ላይ እየሰሩ መሆኑንም ወይዘሮ ወሰነች ተናግረዋል።
በውሃ እና በውሃ ተቋማት ግንባታም በአነስተኛ መኖ ተቋማት እና በአማራጭ ውሃ አጠቃቀም ዙሪያ እንዲሁም በሴቶች እና ህጻናት መብቶች በኢኮኖሚ ተጠቂሚ እንዲሆኑ የድጋፍ ስራዎች እያከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ የፖለቲካ እና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በርካታ የመልማት ፍላጎቶች መኖራቸውን ጠቁመው በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ የልማት ስራዎች በመንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች መታገዛቸው በጥንካሬ የሚታይ ተግባር ነው ብለዋል።
ለዚህም ድርጅቶችን የመደገፍ ስራ ተጠናክሮ መሰራት አለበትም ብለዋል።
የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ነጻ እና ገለልተኛ ሆነው ከተሰጣቸው ተልእኮ ሳይወጡ ሚናቸውንም እንዲወጡ እድል የሰጠ ነውም ብለዋል።
በውይይቱ የሲቪክ ማህበራቱ እያከናወኑ ያሉት ተግባራትንም በየዞኖቹ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ
ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የልማት፣ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ሂደት ለማፋጠን ድርሻው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ