የቢላሃሪዚያ እና አንጀት ጥገኛ ትላትሎች ማስወገጃ የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ዕደላ ዘመቻ ማስጀመሪያ የአመራር ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የህክምና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሉት፤ በተለይ ተጋላጭ ለሆኑ የክልሉ አካባቢዎች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የመድኃኒት ዕደላ ዘመቻ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቋል።
በመሆኑም ትኩረት የሚሹ ሐሩራማ በሽታዎችን ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
የዚህ መድረክ ዋና ዓላማውም ከህዳር ወር መጀመሪያ ጀምሮ የማህበረሰብ አቀፍ መድኃኒት ዕደላ የዘመቻ ሥራዎች በትኩረትና በጥራት ለመስራት እንደሆነም ተመላክቷል።
ትኩረት የሚሹ ሐሩራማ በሽታዎች፣ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎችና የቢላሃሪዚያ በሽታዎች መከላከያ የማህበረሰብ አቀፍ የመድኃኒት ዕደላ የአመራር ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ሰለሞን አላሶ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።