የወላይታ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ የስራ ዕድል ፈጠራ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ዙሪያ ያዘጋጀዉ ዞናዊ ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ዶ/ር ዳንኤል ዳሌ፤ መንግስት ስራ አጥነትና ሥር የሰደደ ድህነት ለመቀነስ በዕድገት ተኮር የስራ ዘርፎች ትኩረት በመስጠት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ከሀብት ብክነት የፀዳ እና በተጨባጭ ውጤት የሚለካ ቅንጅታዊ አሠራር በመፍጠር በርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ በመሆን ኑሯቸውን ማሻሻላቸውን ጠቅሰዋል።
ለወጣቶች ችግር ፈችና ፈጠራ ላይ የተመሰረተ እንዲሁም በዞኑ ባለው ፀጋ ልክ ካለው ስራ አጥነት አንጻር ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጧል ብሎ መውሰድ አይቻልም ያሉት ምክትል አስተዳዳሪው፤ ችግሩን ለመቅረፍ በበጀት ዓመቱ ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባል ብለዋል።
የተለዩ ወጣቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ከሁላችንም የሚጠበቀውን ኃላፊነት መውጣት አለብን ሲሉም በአጽንኦት አሳስበዋል።
የወላይታ ዞን ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቱ ጳውሎስ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዋና ዋና አቅጣጫዎችን በመከተል ከ105 ሺህ በላይ የሥራ ፈላጊ ወጣቶች መለየታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡ በቀሌች ጌቾ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ
ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የልማት፣ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ሂደት ለማፋጠን ድርሻው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ