ፕሮፌሰር ነጋ አሰፋ የተወለዱት በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አሰላ ከተማ ነው፡፡ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በልማት በህብረት፤ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጭላሎ ተራራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል፡፡
ከጅማ ዩኒቨርስቲ በነርስነት ከዚያም በህብረተሰብ ጤናና ስነ ተዋልዶ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡
ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በስነ ተዋልዶ፤ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ወስደዋል፡፡
ከለንደን ስኩል ኦፍ ሀይጅን ደግሞ በዓለም አቀፍ የጤና አመራር በሰርቲፊኬት ተመርቀዋል፡፡
በ1985 በአሰላ የነርሲንግ ትምህርት ቤት በክሊኒካል ሱፐርቫይዘርነት ስራ የጀመሩ ሲሆን በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የአመራር ቦታዎችም አገልግለዋል።
ፕሮፌሰር ነጋ አሰፋ 157 የተለያዩ የምርምር ፅሁፎችን በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ማሳተማቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ናቸው፡፡
ፕሮፌሰር ነጋ አሰፋ በጤናው ዘርፍ የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ26ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡
እሳቸው በጤናው ዘርፍ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች አርአያ በመሆኑ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ ጥላሁን ከበደ እጅ የላቀ የሙያ አገልግሎት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በተጨማሪም አቶ ደረጀ አብደላ፣ ዶክተር ክብሮም ገ/ስላሴ፣ ቢኒያም ተሻለ ላበረከቱት በጎ ተግባር ተሸላሚ ሆነዋል።
ዶክተር ዘለቀ ቆበ፣ ዶክተር ጥሩወርቅ ፍቃዱ፣ አቶ በላይ እንዳሻው፣ ሲስተር ፍቅርተ አበራ፣ ዶክተር ሲሳይ ይፍሩ፣ ፕሮፌሰር ዳምጤ ሽመልስ፣ ዶክተር ማስረሻ ተሰማ፣ ፕሮፌሰር ሀይለሚካኤል ደሳለኝም ተሸላሚዎች ነበሩ።
አዘጋጅ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የነዳጅ እና ቤንዚን ምርቶች ስርጭት ላይ የሚስተዋለውን ኢፍትሃዊነት ለመቅረፍ ጠንከር ያለ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ አስታወቀ
ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለፀ
ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የልማት፣ የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ሂደት ለማፋጠን ድርሻው ከፍተኛ እንደሆነ ተገለፀ