ሀዋሳ፡ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በላስካ ከተማ አስተዳደር ከ1 ሺህ 100 በላይ የ45 ቀን ጫጩቶች ለከተማው ማሕበረሰብ ስርጭት ተካሂዷል።
የላስካ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ኃይሌ ”አንድ እንቁላል ከቤቴ አላጣም” በሚል መሪ ቃል ከዚህ ቀደም በአንደኛ ዙር የክትባት ግዜያቸውን የጨረሱና ለእድገት ብቁ የሆኑ የ45 ቀን ጫጩቶችን ለዚሁ ዓላማ ብቻ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ሁለቱም ቀበሌያት ከ140 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ በመሰብሰብ ስርጭት መደረጉን አመላክተዋል።
በዛሬው ዕለትም ለ2ኛ ዙር በተካሄደው የ45 ቀን ጫጩት ስርጭት ከ200 ሺህ ብር በመሰብሰብ ከ1ሺህ 100 በላይ የ45 ቀን ጫጩቶችን ለከተማው ማሕበረሰብ ማሰራጨት መቻላቸውን ገልፀዋል።
የስጋ እና የእንቁላል ዶሮ በብዛት በማርባት ወደ ገበያ የሚቀርበውን የምግብ አማራጮችን በማስፋት በምግቦች ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት በመቀነስ የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል እንዲሁም በተመጣጠነ የምግብ ስርዓት የዳበረ የአመጋገብ ዘይቤን ለመገንባት የዶሮ መንደር ምስረታ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ጳውሎስ ገልጸዋል።
የላስካ ከተማ ነዋሪዎችም በከተማችን ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ ያለው ይህ የሌማት ትሩፋት ሥራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውና በአንደኛ ዙር በተደረገው ስርጭት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ አወል ከድር – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ