አመራሩ አገልጋይነትን በመላበስ የሚጠበቅበትን ህዝባዊ ኃላፊነትን እንዲወጣ የስልጠናው አበርክቶ የጎላ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናግረዋል::
በስልጠናው ከዞኑ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ከደቡብ ምዕራብ ክልል መዋቅር፣ ከዞኑ አስር ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ400 በላይ ሰልጣኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል አቶ አላሮ ሌንጫ፣ መ/ር በቀለ ጦና እና አቶ ማርቆስ ቡልቻ በጋራ በሰጡን አስተያየት በስልጠናው የቀሰሙትን እውቀት እና ክህሎት በተግባር በማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአገልጋይነት ስሜት ለመወጣት ዝግጁ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
ስልጠናው እንደ ሀገር በፓርቲው መሪነት የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ በማስፋት እንዲሁም የጋራ ሀገራዊ ትርክትን በመፍጠሩ በኩል ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሰልጣኞቹ ለቀጣይ በተሰማሩባቸው የሥራ መስኮች ኃላፊነትን በአገልጋይነት ስሜት ለመወጣት ለተግባር ማነሳሻ ስልጠና ነውም ብለዋል።
ስልጠናው ኃላፊነትን በተገቢው ለመወጣት አቅም የሚሆን ስልጠና ነው ያሉን የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊና የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታርኩ አካሉ ናቸው።
ያለውን ጸጋ በመለየት እንዲሁም በአግባቡ ለመጠቀም የስልጠናው አስተዋጽኦ የላቀ ስለመሆኑ አንስተወል።
በመሆኑም በስልጠናው የቀሰሙትን ተሞክሮ በማስፋፋት እና ገቢራዊ በማድረግ ወደ ተግባር የሚገባበት ነውም ብለዋል።
ዘጋቢ: አዲስአለም ታዬ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ